BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
መከላከያ ሠራዊት ጄነራል ምግበይ ኃይለ ላይ ያቀረበውን ክስ የትግራይ የሰላምና የጸጥታ ቢሮ "ኃላፊነት የጎደለው ነው" አለ
የትግራይ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ብርጋዲየር ጄነራል ምግበይ ሃይለን "ለፋኖ ድጋፍ ይሰጣሉ" የሚለውን ጨምሮ ሌሎችም ያቀረባቸውን ክሶች ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲል ወቀሰ።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በፌስቡክ ገጹ፤ የትግራይ ኃይሎች አመራር የሆኑትን ብርጋዲየር ጄነራል ምግብ ሃይለን "ግብረ አበሮቹ አደራጅነትና አይዞህ ባይነት ዘመቻ አንድነት በሚል ስያሜ ፋኖ በተለያዩ ክልል የዞን ወረዳዎች ትንኮሳ ለመፈጸም ሞክሯል" በሚል መግለጫ አውጥቷል።ብርጋዲየር ጄነራል ምግበይ ሃይለ ከፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
አስፈላጊ እየሆነ ስለመጣው ፋይዳ መታወቂያ ሊያውቋቸው የሚገቡ 8 ጉዳዮች
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 21/2015 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን አጽድቆ ኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያን ከሚጠቀሙ አገራት መካከል እንድትካተት በር ከፍቷል።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ተቋማት ለሚሰጡት አገልግሎት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን በአስገዳጅ ጥቅም ላይ እንዲውል በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ። ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የተያያዙ ሊያውቋቸው ለሚገቡ ስምንት ወሳኝ ጥያቄዎች ምላሽ እነሆ . . .
የቤንዚን የችርቻሮ ዋጋ በ11 ብር ጨመረ
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትናንት ይፋ ባደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 112 ብር ከ67 ሳንቲም ደረሰ። የነጭ ናፍጣ ዋጋ ደግሞ የዘጠኝ ብር ገደማ ጭማሪ ተደርጎበታል።
'ምግብ ተቆጣጥሮኝ ነበር'፡ 191 ኪሎግራም በመቀነስ ከሞት አፋፍ የተመለሰው ሰው
አዮን ፖላርድ ሆስፒታል አልጋ ሲይዝ 286 ኪሎግራም ነበር የሚመዝነው። ኩላሊቱ መሥራት እያቆመ ነበር። ለአንድ ቀንም በሕይወት ስለመቆየቱ እርግጠኛ አልነበረም። በወቅቱ 27 ዓመቱ ነበር።
በስኮትላንድ በታዳጊው አሜን ተክላይ ግድያ ሶስተኛ ተጠርጣሪ ተያዘ
በስኮትላንድ፣ ግላስጎው ነዋሪ የነበረው ታዳጊ አሜን ተክላይ ግድያ ጋር በተያያዘ ሶስተኛ ተጠርጣሪ ተያዘ።
ከአሜሪካ የተባረሩት የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር በአገራቸው ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
የትራምፕን አስተዳደር አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ከአሜሪካ እንዲባረሩ የተደረጉት የደቡብ አፍሪካው አምባሳደር በአገራቸው ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
የቱርኩ ፕሬዝደንት ተቀናቃኛቸውን ማሰራቸውን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ተፋፋመ
የፕሬዝደንት ጣይብ ረሲፕ ኤርዶዋን ቀንደኛ ተቀናቃኝ በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተከትሎ በመላው ቱርክ የተነሳው ከፍተኛ ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል።
እስራኤል የጋዛው ሆስፒታል ላይ ባደረሰችው ጥቃት በህክምና ላይ የነበሩ የሐማስ ኃላፊ ተገደሉ
በኻን ዩኒስ ግዛት ናስር ሆስፒታል ላይ በደረሰው ጥቃት የሐማስ የፋይናንስ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ኢስማኢል ባርሁም መገደላቸው ተሰምቷል።
በአንድ ወቅት በሩሲያ ሥር የነበረው የአሜሪካ ደሴት
ኡናላስካ ደሴት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ወታደራዊ መቀመጫ ነበር። ፓስፊክ ውቅያኖስና ቤሪንግ ባሕር የሚገናኙበት ቦታ ላይ ይገኛል። ከሰሜን አሜሪካ ወደ ሰርቢያ ሲጓዙ ነው ይህንን የአሜሪካ ደሴት የሚመለከቱት።
ቴክኖሎጂ በረቀቀበት ዘመን የመሬት መንቀጥቀጥን መገመት ለምን ከባድ ሆነ?
የዘርፉ ሳይንቲስቶ ርዕደ መሬትን መተንበይ ፈፅሞ የማይታሰብ ነው ይላሉ። የመሬት መንቀጥቀጥ መገመት አለመቻሉ ነው አስፈሪ የሚያደርገው።
የሱዳን ጦር የፕሬዚደንቱን ቤተ መንግሥት መልሶ መቆጣጠሩ የአገሪቱን ጦርነት አቅጣጫ ይቀይራል?
የሱዳን ጦር ወታደሮች የፕሬዝዳንቱን ቤተ መንግሥት መቆጣጣራቸውን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ካርቱም የሚያሳዩት ፈንጠዝያ እንዲሁም በቅርብ ወራት ውስጥ የተለያዩ ግዛቶችን መቆጣጠራቸው ወሳኝ የማጥቃት እርምጃ ላይ መሆናቸውን ያሳያል። የሱዳን ጦር ኃይሎች በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ ዋና ከተማይቱን መቆጣጠር ተስኗቸው ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) እጅ ፈልቅቆ ለማውጣት ለሁለት ዓመታት ሲዋጉ ቆይተዋል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አነጋጋሪ ጉዳይ
ኤርትራ በትግራይ ክልል በተፈጠረው ቀውስ "ምንም ሚና" የለኝም አለች
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ፤ አስመራ በህወሓት እና በትግራይ ክልል "ጊዜያዊ አስተዳደር እየተካሄደ ባለው ግጭት" ውስጥ "ምንም አይነት ሚና" እንደሌላት ተናገሩ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ "የጎረቤቶቿን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንድታከብር" ግፊት እንዲደረግባት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ጥያቄ አቅርበዋል።
በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ክፉኛ አቁስላ፣ ማርካ ያከመችው የጁባላንዱ ፕሬዚዳንት ማዶቤ
"የብዙ ኢትዮጵያዊ ደም ነው የወሰደው። የኢትዮጵያ ደም ነው ያለህ እንለዋለን" ይህ በሶማሊያ የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ለአሁኑ የጁባላንድ ግዛት ፕሬዚዳንት ማዶቤ በቀልድ መልኩ ጣል ያደርጉላቸው ነገር ነው። ይህ በቀልድ የተለወሰ መሪር እውነታ ነው። እውነታው የሶማሊያዋን ራስ ገዝ ጁባላንድን ላለፉት 12 ዓመታት ያስተዳደረው ማዶቤ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ጦር ክፉኛ ቆስሎ በአዲስ አበባ ህክምና አድርጓል።
የኢትዮጵያ መንግሥት አንደኛው የህወሓት ክንፍ ከውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለው ሲል ከሰሰ
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት አንደኛው የህወሓት ክንፍ የአገሪቱ ተቀናቃኝ ከሆኑ የውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እና ትብብር አለው በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰሰ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጤሞቲዮስ ይህንን ያሉት አርብ አዲስ አበባ ውስጥ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በክልሉ ስላለው ሁኔታ ለዲፕሎማቶች ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ነው።
"ለምንድን ነው ከትግራይ የምሸሸው? . . . እመለሳለሁ" አቶ ጌታቸው ረዳ
በትግራይ በህወሓት አመራሮች ያለው አለመግባባት ተባብሶ ወደ ኃይል እርምጃ እያመራ ይገኛል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ክስተት "እብደት" በማለት ድርጊቱ ክልሉን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊወስደው ይችላል ሲሉ እያስጠነቀቁ ነው። ባለፉት ቀናት ከተከሰቱን ሁኔታዎች ጋር አቶ ጌታቸው የት እንዳሉ፣ የፌደራል መንግሥት ድጋፍን ስለመጠየቃቸው እና ስለሌሎችም ጉዳዮች ለቢቢሲ ኒውስ ምላሽ ሰጥተዋል።
መቀለ አቅራቢያ በምትገኘው አዲጉዶም ከተማ የተከሰተው ምንድን ነው?
ማክሰኞ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም. ከመቀለ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው አዲጉዶም ከተማ፣ በደብረፅዮን ገብረሚካኤልን (ዶ/ር) በሚመራው የህወሓት ክንፍ ይደግፋሉ የተባሉ የትግራይ ኃይል አባላት በንፁኅን ዜጎች ላይ ተኩስ ከፍተው አራት ሰዎች ማቁሰላቸውን ነዋሪዎች እና ተጐጂዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ፑቲን ከዩክሬን ጋር ለሚደረግ የተኩስ አቁም ከበድ ያሉ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጡ
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ጋር እንዲደረስ የታቀደውን የተኩስ አቁም ሃሳብ እንደሚስማሙበት ቢገልጹም፤ በርካታ "ጥያቄዎች" የጫሩ ከባድ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል።
የኡጋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ 'ከአገራቸው አታልለው ያመጧትን" ወጣት በዩኬ በባርነት በማሰራት ጥፋተኛ ተባሉ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዲሁም የኡጋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ከአገራቸው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም "አታልለው ያመጧትን" ወጣት በመኖሪያ ቤታቸው በባርነት እንድትሰራ በማስገደድ ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ።
አቶ ጌታቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ማህተም ከነጠቀ አካል" ጋር እንዳይደራደሩ ጠየቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ "ለራሱ የግል እና የቡድን ጥቅም ሲባል የሕዝብን ሠላም፣ የፕሪቶሪያን ስምምነት፣ የአገሪቱን መረጋጋት እንደ መያዣ ከተጠቀመ አካል" ጋር እንዳይደራደሩ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ጠየቁ።ክፍፍል ውስጥ በገቡት የህወሓት ክንፎች ምክንያት ቀውስ ውስጥ የገባውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሚመሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን ያሉት ሐሙስ መጋቢት 4፤ 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
ከየፈርጁ
ኢንሱሊን መላመድ ምንድን ነው? በፆም ወቅትስ እክል ይፈጥራል?
በጡንቻ፣ በስብ እና በጉበት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት ለኢንሱሊን መስጠት ያለባቸውን ምላሽ ሲያስተጓጉሉ ኢንሱሊን መላመድ ተፈጥሯል ማለት ነው። ከደም ውስጥ ጉሉኮስ ወስዶ ማከማቸት እንዲሳናቸው ያደርጋል።
በርካታ የሰላም ስምምነቶች በሳዑዲ አረቢያ እና በኳታር የሚካሄዱት ለምንድን ነው?
ዛሬ ማክሰኞ የአሜሪካ እና የዩክሬን ባለስልጣናት በሳዑዲ አረቢያ ከሩሲያ ጋር የሰላም ስምምነት ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ያደርጋሉ።አገሪቱ ለዚህ የሰላም ውይይት የተመረጠችው መሪዋ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን እና ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባላቸው ጠንካራ ግንኙነት የተነሳ ነው። ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ዓለም አቀፍ የሰላም አደራዳሪ እንዲሆኑ የተመረጡት ለምንድን ነው? በመካከላቸው ቁርሾስ ፈጥሮ ይሆን?
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?
በርካታ አፈታሪኮች፣ ምልኪዎች እና ትንግርቶች ያሏት ሙሉ ጨረቃ
ሙሉ ጨረቃ በምትታይበት ወቅት አስገራሚ ክስተቶች እንደሚፈጠሩ ለዘመናት በርካታ አፈ ታሪኮች ተነግረዋል። አማልክት የሚገለጡበት፣ ሰዎች ወደ ተኩላነት መቀየር፣ አዕምሯቸውን የሚስቱበት ሌላም ሌላም . . . ሙሉ ጨረቃ ስትታይ የሚካሄዱ ፌስቲቫሎች፣ ምልኪዎች ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ባለው ዘመን ቀጥለዋል። እነዚህ ሁሉ ምን ያህል እውነትነት አላቸው?
ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሴቶች የሆኑባቸው አገራት፤ ሴቶች እና ፖለቲካ
አንዳንድ አገራት የሴቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማጎልበት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በማድረግ ከመሪነት ቦታ ላይ ለመድረስ ችለዋል። አሜሪካ እና ጃፓንን የመሳሰሉ ያደጉ እና በዴሞክራሲ የዳበረ ልምድ ያላቸው አገራት ግን እስካሁን አንድም ሴት ፖለቲከኛ ከመሪነት መንበር ላይ ለመውጣት አልቻለችም። በተቃራኒው ባርቤዶስን የመሳሰሉ ጥቂት አገራት ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዝዳንት ለማግኘት ታድለዋል።
ከቤት ሠራተኝነት እስከ ሆቴል ባለቤትነት - የአዲሲኒያ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤት
አዲስ ገብረማርያም የልጅነት ሕይወቷ፣ እጅግ ከባድ እና ውስብስብ ነበር። በኢኮኖሚ ችግር፣ በስደት እና በጦርነት ምክንያት በፈተና የተሞላ ሕይወት ማሳለፏን ታስታውሳለች። ቤተሰቦቿ መሠረታዊ ነገሮች ለሟሟላት ይቸገሩ ነበር። የበኩር ልጅ በመሆኗ ደግሞ ሁሉም ዓይነት ኃላፊነቶች ጫንቃዋ ላይ የወደቀው በእርሷ ላይ ነው።
አጃኢብ!
በህሙማን ላይ የወሲብ እና የቁማር ሱስ ያስከተለው መድኃኒት
በዩናይትድ ኪንግደም ከቁጥጥር የወጣ የሰውነት እንቅስቃሴ ችግር የገጠማቸው ሴቶች የተሰጣቸው መድኃኒት ያለው የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልተነገራቸው ለቢቢሲ ገለጹ። ሕክምና ከወሰዱ መካከል 20 ሴቶች ለቢቢሲ እንደገለጹት የተሰጣቸው መድኃኒት "አሉታዊ ወሲባዊ ባህሪ" እንዲያዳብሩ የሚያደርግ መሆኑ አልተነገራቸውም።
የእንጀራ ልጇን ለ20 ዓመታት አግታለች የተባለችው አሜሪካዊት በቁጥጥር ስር ዋለች
ለ20 ዓመታት ያህል በእንጀራ እናቱ ታግቶ የነበረው አሜሪካዊ የተያዘበት ክፍል ላይ እሳት በመለኮስ ማምለጡን ባለስልጣናቱ ተናገሩ። ቃጠሎውን ተከትሎ የመጡ ባለስልጣናት በጠባብ ክፍል ታግቶ ነበረውን የ32 ዓመቱ ግለሰብ መታደጋቸውም ተነግሯል።
ቪዲዮ, ሃዲድ ላይ ተኝቶ ባቡር በላዩ ላይ ከሄደበት በኋላ በተአምራዊ ሁኔታ የተረፈው ግለሰብ, ርዝመት 0,56
በፔሩ ዋና ከተማ ሊማ ውስጥ አንድ ግለሰብ ሰክሮ በከተማዋ ውስጥ በሚያቋርጥ የባቡር ሃዲድ ላይ ተኝቶ ሳለ ባቡሩ በላዩ ላይ ሄዶበታል። ነገር ግን ግለሰቡ ከባድ ጉዳት ሳይደርስበት ከአሰቃቂው አደጋ ለመትረፍ ችሏል። የአካባቢው አስተዳደር ግለሰቡ በተአምራዊ ሁኔታ የተረፈበትን አሰቃቂ አደጋ የሚያሳይ ቪዲዮን አጋርቷል።
"'ወንድ ነሽ ተብዬ' ከሴቶች እግር ኳስ ተገለልኩ" መሳይ ተመስገን
መሳይ ተመስገን በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ውስጥ ድንቅ ብቃት አለቸው ከሚባሉት መካከል ትጠቀሳለች። እግር ኳስን በሰፈር ውስጥ የጀመረችው መሳይ እስከ ኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተጫውታለች። የት ትደርሳለች የተባለቸው ተጫዋች “ጾታዋ ልክ” አይደለም በሚል ከእግር ኳስ ጋር ተለያይታለች።
በምሥራቅ እስያ በርካቶች ሃይማኖታቸውን መተው ወይም መቀየርን ለምን መረጡ?
በምሥራቅ እስያ ውስጥ በሚገኙ አገራት የሚኖሩ በርካታ ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው በመውረስ ሲከተሉ የቆዩትን ሃይማኖት እርግፍ አድርገው እየተዉ መሆናቸውን ጥናት አመለከተ። የተወሰኑት ፊታቸውን ወደ ሌላ እምነት ሲያዞሩ፤ አብዛኞቹ ግን ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር ቁርኝት እንዳይኖራቸው የሚፍልጉ ናቸው። ይህ መጠንም ከተቀረው ዓለም ይልቅ በምሥራቅ እስያ ከፍተኛ ነው። ምክንያቱ ምንድን ነው?
"ቲክቶክ በአፍሪካ ሕጻናትን በሚያካትቱ ወሲባዊ ቀጥታ ሥርጭቶች ትርፍ እያገኘ ነው"
ቲክቶክ ገና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ በሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች በሚከናወኑ የወሲባዊ ይዘቶች የቀጥታ ሥርጭቶች ትርፍ እያገኘ መሆኑን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ምዕራባውያንን ያሳሰበው የፑቲን ምሥጢራዊ የጥቃት መሳሪያ
ለዓመታት በጥርጣሬ እና በውጥረት ውስጥ የቆየው የሩሲያ እና የምዕራባውያኑ ግንኙነት ዩክሬን ውስጥ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ለይቶለት ወደ ግጭት እንዳይገባ ስጋት ከተፈጠረ ሦስት ዓመታት ሆኖታል። ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ፊት ለፊት ከምታደርገው ጦር ባሻገር ከምዕራባውያን ጋር በሌላ ግንባር የአሻጥር ጦርነት እያደረገች ነው ሲል የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች ማኅበር (ኔቶ) ያምናል። ለዚህም ሩሲያ ምሥጢራዊ ጥቃቶችን እየፈጸመች እና እየተዘጋጀች ነው በሚል ትከሰሳለች።
ቪዲዮ, የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አለባበስ ከሌሎች መሪዎች ለምን የተለየ ሆነ?, ርዝመት 1,59
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከከፈተችበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ሦስት ዓመታት በታላላቅ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ሳይቀር በተለየ አለባበስ የሚቀርቡት የፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አለባበስ አነጋጋሪ ሆኗል። ዋይት ሐውስ ውስጥ ለምን ሥልጣናቸውን የሚመጥን ልብስ እንደማይልበሱ እና ሙሉ ልብስ እንዳላቸው የተጠየቁት ዜሌንስኪ በኃይለ ቃል ምላሽ ሰጥተዋል። ለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ እንደሌሎቹ የዓለም አገራት መሪዎች ለምድን ነው ሙሉ ልብስ የማይለብሱት?
አሜሪካ ከ15 ዓመታት በኋላ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው በአልሞ ተኳሾች የሚፈጸም የሞት ቅጣት
በአሜሪካ ከአስራ አምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ አንድ ሞት የተፈረደበት እስረኛ በአልሞ ተኳሾች በጥይት አርብ ዕለት ተገድሏል። የደቡብ ካሮላይና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብራድ ሲግሞን የተሰኘው ፍርደኛ የሞት ቅጣቱ በጥይት ተፈጻሚ እንዲሆንበት ብይኑን ረቡዕ ዕለት ነበር ያስተላለፈው።
ሞታቸውን ለማፋጠን የሚጾሙ ሃይማኖተኞች እንዳሉ ያውቃሉ?
በዓለማችን ላይ ያሉ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጥንካሬ፣ ለአካላቸው ጤንነት እንዲሁም ከሞት በኋላ በሚኖረው ዓለም መልካም ነገሮችን ለማግኘት ይጾማሉ። በሕንድ ያሉት የጄይን እምነት ተከታዮች ግን በዕድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሞታቸውን ለማፋጠን አጥብቀው ይጾማሉ።
የተመለሱ ጥያቄዎች
በሴቶች እና በሕጻናት ጤና ላይ ዓለም አቀፋዊ ፈተና የሆነው የአይረን ንጥረ ነገር እጥረት
የአይረን (ብረት) ንጥረ ነገር እጥረት በዓለም በሰዎች ላይ ለሚከሰት የአካል ጉዳት መንስኤዎች መካከል አንዱ ነው። ነገር ግን እጥረቱ መቼ ችግር እንደሚሆን እና ለማከም ጥሩ የሆነው መንገድ ግልፅ አይደለም። ይህንን ለጤና አስፈላጊ የሆነውን ንጥረ ነገር ለማሟላት ምን ማድረግ እንችላለን?
ኢሉሚናቲዎች መነሻቸው ከየት ነው? ዓለምንስ በምሥጢር 'ይቆጣጠራሉ'?
"ኢሉሚናቲዎች በምሥጢር ዓለምን ተቆጣጥረው አዲስ ሥርዓት ሊዘረጉ ነው" የሚለው መላ ምት ለዓመታት ሲሰማ ቆይቷል። የዚህ ሃሳብ መነሻ በአውሮፓውያኑ 1960ዎቹ የነበረ ልብ ወለዳዊ ክስተት ነው። ጀርመን የነበረው 'ኢንላይትመንት ኢራ' ወይም የዕውቀት ብርሃን ዘመን ከኢሉሚናቲ መነሻ ጋር ይተሳሰራል።
በረመዳን የፆም ወቅት የትኞቹን ምግቦች መመገብ፣ የትኞቹንስ መተው ይመከራል?
ረመዳን የፆም ወቅት ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነው። ከማለዳ ጀምሮ አስከ ምሽት ድረስ ምግብ ሳይቀመስ የሚቆይበት የፆም ጊዜ የመጀመሪያ ቀናት ለአንዳንዶች ፈታኝ ነው። በፆሙ ወቅት መደበኛ እንቅስቃሴያችንን እያደረግን ያለድካም ለመቆየት የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በዚህ ወቅት ምን ዓይነት ምግቦችን መመገብ፤ የትኞችንስ ማስቀረት አለብን?
ወባን ለመሳሰሉ በፓራሳይት ለሚመጡ በሽታዎች ክትባት ማዘጋጀት ለምን ፈታኝ ሆነ?
በታዳጊ አገራት ውስጥ በስፋት የሚሠራጩትን እና በርካቶችን ለሞት እና ለጉዳት የሚዳርጉትን ወባን የመሳሰሉ በፓራሳይት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ክትባቶችን ማግኘት አዳጋች ሆኖ ቆይቷል። በቅርቡ ለወባ መከላከያ የሚሆን ክትባት ከዓመታት ልፋት በኋላ ዕውን ሆኗል። ለመሆኑ ለእንዲህ ዓይነት በሽታዎች ክትባት ማግኘት ለምን ፈታኝ ሆነ?
የሚደክምዎ እና ሰውነትዎ ድንገት የሚዝል ከሆነ ኃይል ለማግኘት የሚረዱ 5 ቀላል መፍትሄዎች
አንዳንድ ሰው ቶሎ ይደክመኛል ይላል። አንዳንድ ሰው “ምግብ ስበላ ራሱ ይደክመኛል” ይላል። አንዳንዱ ደግሞ ቀኑን ገና ሳያጋምሰው “እንቅልፍ-እንቅልፍ ይለኛል” ይላል። ያለምክንያት ይደምዎታል? ሰውነትዎ ድንገት ይዝላል? እነዚህን 5 ቀላል የምግብ ለውጦችን ይሞክሩ።
የእርጅና ምልክቶችን የሚያዘገየው እና በቆዳችን ጤንነት ላይ ጉልህ ውጤት የሚኖረው ምርምር
ተመራማሪዎች የእርጅና ምልክቶችን ለማዘግየት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ የተባሉ ሳይንሳዊ ግኝቶችን ይፋ አድርገዋል። የተመራማሪዎቹ ቡድን፣ የሰው አካል ከስቴም ሕዋስ እንዴት ቆዳን እንደሚፈጥር እንዲሁም የተወሰነ መጠን ያለው ቆዳን በቤተ ሙከራ ውስጥ ማምረት እንደሚቻል ደርሶበታል።
የምግብ ሸቀጦችን ትንሽም ቢሆን በጅምላ እና በችርቻሮ መሸመት ያለው ጥቅም ሲሰላ
የምግብ ሸቀጦችን በጅምላ መግዛት ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው። አንደኛ ወጪ ይቆጥባል። ሁለተኛ ለአካባቢ ጥበቃ ያግዛል። ሉሲ በየጊዜው ደጋግሞ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ቃሪያ መግዛት አንድ ጊዜ ከመግዛት አንጻር ያለውን ልዩነት ካወቀች በኋላ ወርሃዊ ወጪዋን እንዳስተካከለች ትናገራለች።
ሞባይላችን እንቅልፋችንን እያደናቀፈ መሆኑን ልብ ብለናል? ሌሊት ለምን እንቅልፍ እምቢ ይለናል?
ሌሊት ለምን እንቅልፍ እምቢ ይለናል? ምን እናድርግ?
በልምምድ የሚዳብረው በርካታ ፈዋሽ ጠቀሜታ ያለው የአተነፋፈስ ጥበብ
የአተነፋፈሳችን ሁኔታ በጤናች ላይ የራሱ የሆነ ውጤት አለው። የተለያዩ የአተነፋፈስ ዘዴዎችን በመጠቀም በሰው ልጆች ጤና ላይ ለውጥ ማምጣት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የታወቀ ነው።
ሌላ ዕይታ
ከማኅደራችን
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ
ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ (ዶክትሬት) የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እና ታሪክን በሚወክሉ በአምስት መምህራን ተወክሎ ቀርቧል።
"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።
ቪዲዮ, በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።
ለአራት ዓመታት ከኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ጋር በመኖር የተቀረጸው ፊልም፡ ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’
የዘጋቢ ፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጆች ማክስ ደንካን እና ዘንየን ዩ ናቸው። ከፕሮዲውሰሮቹ አንዷ ታማራ ማርያም ዳዊት ናት። ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’ በዋርሶው ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል፣ በትሪቤካ ፊልም ፌስቲቫል፣ በሼፊልድ ኢንተርናሽናል ዶክመንተሪ ፌስቲቫል እና በሌሎችም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ዕውቅና አግኝቷል። ፊልሙ የቻይና ባለ ሃብቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ሥራ አጥነትን፣ ባህልን፣ ቤተሰብን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የአርሶ አደሮች የተጠቃሚነት ጥያቄን በዋናነት ይዳስሳል።
የሳንቲም ትዝታዎች - ፕሮፌሰር እሌኒ ዘለቀ ስትታወስ
“ሐኪሞቹ ‘ሰዓት አልቋል’ አሉ። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ይቺን ምድር እሰናበታለሁ።” እነዚህ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ፕሮፌሰር እና የፖለቲካ ሳይንቲስት እሌኒ ሳንቲም ዘለቀ ቃላት ናቸው። ፕሮፌሰር እሌኒ ይህን መልዕክት በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ካስተላለፈች አንድ ሳምንት በኋላ ኒው ዮርክ በሚገኘው ኢስት ኢንድ ሆስፒስ ውስጥ ሕይወቷ አልፏል። ተማሪዎቿ፣ ወዳጆቿ እና የሚያውቋት እሌኒን እና ሥራዎቿን ዘክረዋል።
በቲክቶክ ዘመን ቆዳ አልፍተው፣ ብራና ወጥረው፣ ቀለም በጥብጠው ግዕዝ የሚማሩት የአዲስ አበባ ሕጻናት
አዳጊዎች ናቸው፤ የተገፈፈ የፍየል ቆዳ ያለፋሉ። ይደጉሳሉ። ይጠርዛሉ። ካራ፣ ጉጠት፣ መጥረቢያ. . . ተጠቅመው ቆዳ ያለሰልሳሉ። ቀጨም ተጠቅመው ብራና ይወጥራሉ። ይህን ሁሉ የሚሠሩቱ ርቆ ከሚገኝ መንደር ያሉ ቆሎ ተማሪዎች አይደሉም፤ ዘመናይ ከተሜዎች እንጂ። አንዳንዶቹ የቦሌ እና የካዛንቺስ ልጆች፤ አንዳንዶቹ የሳር ቤት እና የሲኤምሲ ተወላጆች ናቸው። ደግሞ ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ መሀል ፒያሳ ላይ ነው።
የኩላሊታችንን ጤና ለመጠበቅ የሚያግዙ 6 ቀላል መንገዶች
በኢትዮጵያ በስፋት እየተስተዋሉ ከሚታዩ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች መካከል የኩላሊት ችግር አንዱ እየሆነ መጥቷል። ወሳኝ ከሆኑት የሰውነት ክፍሎች መካከል አንዱ የሆነው ኩላሊት በተለያዩ ምክንያቶች እክሎች ይገጥሙታል። ነገር ግን የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር እና ጥንቃቄ በማድረግ ጤናማ ኩላሊት እንዲኖረን ማድረግ ይቻላል። ከእነዚህም መካከል ለኩላሊት ጤና የሚረዱ ስድስት ቀላል ጥንቃቄዎችን እነሆነ. . .
የላጤዎች ጉባኤ በቦሌ
በፈረንጅ አፍ ‘ስፒድ ዴቲንግ’ ይባላል። የአማርኛ አቻ የለውም። በአቋራጭ መተጫጨት ነው-ነገሩ። ፖለቲካዊ ቋንቋ ይመስልብናል እንጂ ‘የትዳር ማሳለጫ’ ሊባል ይችላል። ነገሩ ‘የፍቅር-ጉድኝት’ ለመፍጠር የሚደረግ አጭር ጉዞ ነው። የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት አደን እንደመውጣት ያለ ነው። የትዳር አሰሳ. . . የወደፊት ውሃ አጣጭን ለማማለል የሚሰጥ የአምስት ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ምት ነው። የት? አዲስ አበባ ቦሌ ላይ. . .
ምሥሎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዴት ይሠራሉ? ከእውነተኞቹስ እንዴት መለየት ይቻላል?
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) አማካይነት የሚዘጋጁት ምሥሎች ለእውነታ በእጅጉ የቀረቡ በመሆናቸው ምክንያት ትክክለኛ ፎቶዎች ወይም የሰው ልጅ የአእምሮ እና የእጅ ሥራ ውጤት ከሆኑት አንጻር ለመለየት አዳጋች እየሆኑ መጥተዋል። ታዲያ በዚህ ቴክኖሎጂ የተዘጋጁትን ምሥሎች ከእውነተኞቹ እንዴት መለየት እንችላለን?
የተጠጋገኑ እና ኦሪጂናል ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮች እኛንም ስልካችንንም እንደሚጎዱ ያውቃሉ?
ሊበጠስ ጫፍ የደረሰ እና የተጠጋገነ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያን መጠቀም ብዙዎቻችን ምንም ጉዳት የሌለው ይመስለናል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቀ ሲከፋም አሰቃቂ አደጋን ሊያስከትል ይችላል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮችን መጠቀም ምን ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ? ምን ዓይነት ቻርጀሮችን ብንጠቀም ይመከራል?


















































































